ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የመገናኛውን ድንኳን ሥርዓት የመቅደሱንም ሥርዓት የወንድሞቻቸውንም የአሮንን ልጆች ሥርዓት ለመጠበቅ ነበረ።
ዘኍል 3:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌድሶናውያንም በመገናኛው ድንኳን የሚጠብቁት ማደሪያው፥ ድንኳኑም፥ መደረቢያውም፥ የመገናኛው ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጌርሶናውያን ኀላፊነት በመገናኛው ድንኳን ማደሪያውንና ድንኳኑን፣ መደረቢያዎቹን እንዲሁም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ያለውን መጋረጃ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌድሶናውያንም በመገናኛው ድንኳን የሚጠብቁት ማደሪያውን፥ ድንኳኑን፥ መደረቢያውን፥ የመገናኛውንም ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመገናኛው ድንኳን የጌርሾን ልጆች ኀላፊነት የነበረው በመገናኛው ድንኳን፥ ከውጪና ከውስጥ በኩል ባለው መሸፈኛ፥ በመግቢያው ደጃፍ መጋረጃ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጌድሶን ልጆች በምስክሩ ድንኳን የሚጠብቁት ማደሪያውና ድንኳኑ፥ መደረቢያውም፥ የምስክሩ ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥ |
ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የመገናኛውን ድንኳን ሥርዓት የመቅደሱንም ሥርዓት የወንድሞቻቸውንም የአሮንን ልጆች ሥርዓት ለመጠበቅ ነበረ።
ሕዝቅያስም የካህናትንና የሌዋውያንን ሰሞን በየክፍላቸውና በየአገልግሎታቸው አቆመ፤ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ በሮች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ፥ ያገለግሉም ዘንድ፥ ያመሰግኑም ያከብሩም ዘንድ ካህናቱንና ሌዋውያኑን አቆመ።
ነገር ግን በምስክሩ ማደሪያና በዕቃዎች ሁሉ ለእርሱም በሚሆነው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋውያንን አቁማቸው። ማደሪያውንና ዕቃዎችን ሁሉ ይሸከሙ፥ ያገልግሉትም፥ በማደሪያውም ዙሪያ ይስፈሩ።