የጌድሶናውያን ወገኖች ከማደሪያው በኋላ በምዕራብ በኩል ይሰፍራሉ።
የጌርሶን ጐሣዎች በምዕራብ በኩል ከማደሪያው ድንኳን ጀርባ ይሰፍራሉ።
የጌድሶናውያን ወገኖች ከማደሪያው በስተጀርባ በምዕራብ በኩል ይሰፍራሉ።
የጌርሾናውያን ወገን የሚሰፍረው ከድንኳኑ በስተጀርባ በምዕራብ በኩል ነበር።
የጌድሶን ልጆች ከድንኳን በኋላ በባሕር በኩል ይሰፍራሉ።
ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ላይ ቍጣ እንዳይወርድ ሌዋውያን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይስፈሩ፤ ሌዋውያንም የምስክሩን ማደሪያ ይጠብቁ።
ከዚያም በኋላ የመገናኛው ድንኳን በሰፈሮቹም መካከል የሌዋውያን ሰፈር ይጓዛል፤ እንደ ሰፈራቸው ሰው ሁሉ በየስፍራው በየዓላማውም ይጓዛሉ።
ከእነርሱ የተቈጠሩት የወንዶች ሁሉ ቍጥር ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ የተቈጠሩት ሰባት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።
የጌድሶናውያንም አባቶች ቤት አለቃ የዳኤል ልጅ ኤሊሳፍ ይሆናል።