ዘኍል 3:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሌዊን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች በየወገናቸውም ቍጠር፤ ወንዱን ሁሉ ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ቍጠራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሌዋውያንን በየቤታቸውና በየጐሣቸው ቍጠር፤ የምትቈጥረውም አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ ነው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሌዊን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች በየወገናቸውም ቁጠር፤ ወንዱን ሁሉ ዕድሜው አንድ ወር የሞላውንና ከዚያም በላይ ያለውን ቁጠራቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሌዋውያንን በየወገናቸውና በየቤተሰባቸው መድበህ ቊጠር፤ ከተወለደ አንድ ወር የሞላውንና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ ቊጠር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሌዊን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ በየወገናቸውም ቍጠር፤ ወንዱን ሁሉ ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ቍጠራቸው።” |
ሂድ፥ በኢየሩሳሌም ጆሮ ጩኽ፥ እንዲህም በል፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ምሕረት የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስቤአለሁ።
ከሌዋውያንም በየወገናቸው የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው፤ ከጌድሶን የጌድሶናውያን ወገን፥ ከቀዓት የቀዓታውያን ወገን፥ ከሜራሪ የሜራራውያን ወገን።
ከአንድ ወርም ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉ ወንዶች ሁሉ ከእነርሱ የተቈጠሩ ሀያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አልተሰጣቸውምና ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም።