La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 26:57 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከሌዋውያንም በየወገናቸው የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው፤ ከጌድሶን የጌድሶናውያን ወገን፥ ከቀዓት የቀዓታውያን ወገን፥ ከሜራሪ የሜራራውያን ወገን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በየጐሣቸው የተቈጠሩት ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤ በጌርሶን በኩል፣ የጌርሶናውያን ጐሣ፣ በቀዓት በኩል፣ የቀዓታውያን ጐሣ፣ በሜራሪ በኩል፣ የሜራራውያን ጐሣ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከሌዋውያንም በየወገናቸው የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው፤ ከጌድሶን የጌድሶናውያን ወገን፥ ከቀዓት የቀዓታውያን ወገን፥ ከሜራሪ የሜራራውያን ወገን።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከሌዋውያን ነገድ ተወላጆች፦ ጌርሾን፥ ቀዓት፥ ሜራሪና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። የእነርሱም ዘሮች ሊብኒ፥ ኬብሮን፥ ማሕሊ፥ ሙሴ፥ ቆሬና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። ቀዓትም አሞራምን ወለደ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሌዊ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የተ​ቈ​ጠ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ ከጌ​ድ​ሶን የጌ​ድ​ሶ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከቀ​ዓት የቀ​ዓ​ታ​ው​ያን ወገን፥ ከሜ​ራሪ የሜ​ራ​ራ​ው​ያን ወገን።

Ver Capítulo



ዘኍል 26:57
12 Referencias Cruzadas  

የሌዊም ልጆች ጌድሶን፥ ቀዓት ሜራሪ።


የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።


የአሮንም ልጅ አልዓዛር ከፉትኤል ልጆች ሚስት አገባ፤ እርስዋም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደ ወገኖቻቸው የሌዋውያን አባቶች አለቆች ናቸው።


ሌዋውያን ግን በየአባቶቻቸው ነገድ ከእነርሱ ጋር አልተቈጠሩም።


ሌዋውያን ግን እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም።


በብዙዎችና በጥቂቶች መካከል ርስታቸው በዕጣ ትከፈላለች።


የሌዊን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች በየወገናቸውም ቍጠር፤ ወንዱን ሁሉ ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ቍጠራቸው።


የሌዊ ልጆች በየስማቸው እነዚህ ናቸው፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።