ዘኍል 21:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም፦ በምድርህ ላይ እንለፍ፤ ወደ እርሻና ወደ ወይን ቦታ አንገባም፤ ከጕድጓድም ውኃን አንጠጣም፤ ከምድርህ ዳርቻ እስክንወጣ ድረስ በንጉሥ ጐዳና እንሄዳለን ብለው ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልእክተኞችን ላኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ የሚሉ መልእክተኞች ላከ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም እንዲህ ብሎ መልእክተኞችን ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን ላከ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ወደ አሞራውያን ንጉሥ ሲሖን እንዲህ ብለው የሚነግሩትን መልእክተኞች ላኩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም ወደ አሞሬዎናውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን በሰላም ቃል እንዲህ ብሎ መልእክተኞችን ላከ፤ |
የሸሹ ደክመው ከሐሴቦን ጥላ በታች ቆመዋል፥ እሳት ከሐሴቦን ነበልባልም ከሴዎን ወጥቶአል የሞዓብንም ማዕዘን የሤትንም ልጆች አናት በልቶአል።
የእስራኤልም ልጆች የመቱአቸው፥ ከአርኖንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ ያለውን ዓረባ ሁሉ በዮርዳኖስም ማዶ በፀሐይ መውጫ ያለውን አገራቸውን የወረሱአቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፥
ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፥ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥ በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል።
እኔም በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡበት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ፥ ከእናንተም ጋር ተዋጉ፥ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ፥ ምድራቸውንም ወረሳችሁ፥ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው።
እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች አላቸው፦ ግብፃውያን፥ አሞራውያንም፥ የአሞንም ልጆች፥ ፍልስጥኤማውያንም፥ ሲዶናውያንም፥ አማሌቃውያንም፥ ማዖናውያንም አላስጨነቋችሁምን? ወደ እኔም ጮኻችሁ፥ እኔም ከእጃቸው አዳንኋችሁ።