ዘኍል 20:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደዚህ ክፉ ስፍራ ታመጡን ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣችሁን? ዘርና በለስ ወይንም ሮማንም የሌለበት ስፍራ ነው፤ የሚጠጣም ውኃ የለበትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከግብጽ አውጥታችሁ እህል ወይም በለስ፣ ወይን ወይም ሮማን ወደሌለበት ወደዚህ ክፉ ቦታ ያመጣችሁንስ ለምንድን ነው? የሚጠጣ ውሃ እንኳ ይታጣ!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደዚህ ክፉ ስፍራ ልታመጡን ከግብጽ ለምን አወጣችሁን? ለዘርና ለበለስ ለወይንም ለሮማንም የማይሆን ስፍራ ነው፤ የሚጠጣም ውኃ የለበትም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ አውጥታችሁ ምንም ነገር ወደማይበቅልበት ወደዚህ አስከፊ ምድር ለምን አመጣችሁን? በዚህ ስፍራ እህል፥ በለስ፥ ወይንና ሮማን አይገኝም፤ ሌላው ቀርቶ የሚጠጣ ውሃ እንኳ የለም!” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘር ወደማይዘራበት፥ በለስና ወይንም፥ ሮማንም፥ የሚጠጣም ውኃ ወደሌለበት ወደዚህ ክፉ ስፍራ ታመጡን ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣችሁን?” |
ሂድ፥ በኢየሩሳሌም ጆሮ ጩኽ፥ እንዲህም በል፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ምሕረት የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስቤአለሁ።
እነርሱም፦ ከግብጽ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳም በባድማ ጕድጓድም ባለበት ምድር፥ በውኃ ጥምና በሞት ጥላ ምድር፥ ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም።
ደግሞ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር አላገባኸንም፥ እርሻና ወይንም አላወረስኸንም፤ የእነዚህንስ ሰዎች ዓይኖቻቸውን ታወጣለህን? አንመጣም አሉ።
እናንተ በጺን ምድረ በዳ በማኅበሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አልቀደሳችሁኝምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የመሪባ ውኃ ነው።