በሙሴና በአሮን ላይ ተሰብስበው፦ ማኅበሩ ሁሉ እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸውና፥ እግዚአብሔርም በመካከላቸው ነውና እናንተ እጅግ አብዝታችኋል፤ በእግዚአብሔርም ጉባኤ ላይ ለምን ትታበያላችሁ? አሉ።
ዘኍል 16:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገም በእግዚአብሔር ፊት እሳት አድርጉባቸው፥ ዕጣንም ጨምሩባቸው፤ እንዲህም ይሆናል፤ እግዚአብሔር የሚመርጠው እርሱ ቅዱስ ይሆናል፤ እናንተ የሌዊ ልጆች ሆይ፥ እጅግ አብዝታችኋል ብሎ ተናገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም በእግዚአብሔር ፊት እሳትና ዕጣን ጨምሩባቸው፤ እግዚአብሔር የሚመርጠውም ያ ሰው ቅዱስ ይሆናል፤ እናንተ የሌዊ ልጆች፤ ከልክ ያለፋችሁትስ እናንተ ናችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም በጌታ ፊት እሳት አድርጉባቸው፥ ዕጣንም ጨምሩባቸው፤ እንዲህም ይሆናል፤ ጌታ የሚመርጠው እርሱ ቅዱስ ይሆናል፤ እናንተ የሌዊ ልጆች ሆይ! እጅግ አብዝታችሁታል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነርሱም ላይ የከሰል ፍምና ዕጣን አድርጋችሁ ወደ መሠዊያው አቅርቡአቸው፤ ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ማንኛችንን መርጦ ለራሱ እንደ ለየ እናያለን፤ ከልክ ያለፋችሁትስ እናንተ ሌዋውያኑ ናችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገም በእግዚአብሔር ፊት እሳት አድርጉባቸው፤ ዕጣንም ጨምሩባቸው፤ እግዚአብሔርም የሚመርጠው ይህ ሰው ለሌዊ ልጆች ቅዱስ ይሁንላቸው።” |
በሙሴና በአሮን ላይ ተሰብስበው፦ ማኅበሩ ሁሉ እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸውና፥ እግዚአብሔርም በመካከላቸው ነውና እናንተ እጅግ አብዝታችኋል፤ በእግዚአብሔርም ጉባኤ ላይ ለምን ትታበያላችሁ? አሉ።
እኛ ግን፥ በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፥ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና፤
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤