La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 16:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሙሴም ቆሬን፦ ነገ አንተ፥ ወገንህም ሁሉ፥ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁኑ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሙሴም ቆሬን እንዲህ አለው፤ “አንተና ተከታዮችህ እንዲሁም አሮን ነገ በእግዚአብሔር ፊት ትቀርባላችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሙሴም ቆሬን እንዲህ አለው፦ “ነገ አንተ፥ አንተንም የሚከተሉህ ሁሉ፥ አሮንም በጌታ ፊት ተገኙ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሙሴ ቆሬን እንዲህ አለው፦ “ነገ አንተና ሁለት መቶ ኀምሳ ተባባሪዎችህ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን እንድትመጡ፤ አሮንም እዚያው ይገኛል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴም ቆሬን አለው፥ “ማኅ​በ​ር​ህን ለይ፤ ነገ አንተ፥ ማኅ​በ​ር​ህም ሁሉ፥ አሮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዝግ​ጁ​ዎች ሁኑ።

Ver Capítulo



ዘኍል 16:16
8 Referencias Cruzadas  

ሙሴም አሮንን፦ ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ ማንጎራጎራችሁን ሰምቶአልና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ በል አለው።


እግዚአብሔርም ወዲያው ሙሴንና አሮንን ማርያምንም፦ ሦስታችሁ ወደ መገኛኛው ድንኳን ውጡ ብሎ ተናገረ፤ ሦስቱም ወጡ።


ሙሴም እጅግ ተቈጣ፥ እግዚአብሔርንም፦ ወደ ቍርባናቸው አትመልከት፤ እኔ ከእነርሱ አንድ አህያ ስንኳ አልወሰድሁም፥ ከእነርሱም አንድ ሰው አልበደልሁም አለው።


ሁላችሁም ጥናዎቻችሁን ውሰዱ፥ ዕጣንም አድርጉባቸው፥ እያንዳንዳችሁም ጥናዎቻችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት አምጡ፥ ሁለት መቶ አምሳ ጥናዎች፤ አንተ ደግሞ አሮንም ጥናዎቻችሁን አምጡ አለው።


ይህን አሳስባቸው፥ በቃልም እንዳይጣሉ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፥ ይህ ምንም የማይረባ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና።


እነሆኝ፥ በእግዚአሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፥ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንንስ አህያ ወሰድሁ? ማንንስ ሸነገልሁ? በማንስ ላይ ግፍ አደረግሁ? ዓይኖቼንስ ለማሳወር ከማን ጋር እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? እኔም እመልስላችኋለሁ።


አሁንም እግዚአብሔር ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ስላደረገው ጽድቅ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እምዋገታችሁ ዘንድ በዚህ ቁሙ።