ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ተናገሩ፥ በሉአቸውም፥ በዚህ ወር በአሥረኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤት አንድ ጠቦት፥ ለአንድ ቤትም አንድ ጠቦት ይውሰድ።
ዘኍል 15:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ ለእያንዳንዱ ወይፈን ወይም ለእያንዳንዱ አውራ በግ ወይም ለእያንዳንዱ ተባት የበግ ወይም የፍየል ጠቦት ይደረጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱ ወይፈን ወይም አውራ በግ፣ እያንዳንዱ የበግም ሆነ የፍየል ጠቦት በዚህ ሁኔታ ይዘጋጅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለእያንዳንዱም ወይፈን ወይም ለእያንዳንዱ አውራ በግ ወይም ለእያንዳንዱ ተባት የበግ ወይም የፍየል ጠቦት እንዲሁ ይደረጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘እንግዲህ ከእያንዳንዱ ወይፈን፥ አውራ በግ፥ የበግ ወይም የፍየል ጠቦት ጋር የሚቀርበው የእህል ቊርባን ይህ ነው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንዲሁ ለእያንዳንዱ ወይፈን፥ ወይም ለእያንዳንዱ አውራ በግ፥ ወይም ለእያንዳንዱ ተባት የበግ ወይም የፍየል ጠቦት ይደረጋል። |
ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ተናገሩ፥ በሉአቸውም፥ በዚህ ወር በአሥረኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤት አንድ ጠቦት፥ ለአንድ ቤትም አንድ ጠቦት ይውሰድ።
በወሩ መባቻ ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ በዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ ከመጠጡም ቍርባን ሌላ፥ እንደ ሕጋቸው ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርቡ ናቸው።