ዘኍል 15:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት ለተደረገ ቍርባን፥ የኢን መስፈሪያ ግማሽ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን ታቀርባለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን ግማሽ ሂን የወይን ጠጅ አቅርቡ፤ ይህም በእሳት የሚቀርብና ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርገህ፥ የኢን መስፈሪያ ግማሽ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቁርባን ታቀርባለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ግማሽ ሊትር የወይን ጠጅ የመጠጥ ቊርባን አድርገህ ታቀርባለህ፤ ይህም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ የሚሆን የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን በእሳት ለተደረገ ቍርባን፥ የኢን መስፈሪያ ግማሽ ወይን ለመጠጥ ቍርባን ታቀርባለህ። |
አንድ ሌማትም ቂጣ እንጀራ፥ በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄትም የተሠሩ እንጐቻዎች፥ በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ፥ የእህሉንም ቍርባን፥ የመጠጡንም ቍርባን ያቅርብ።
ጡትም በተወ ጊዜ ከእርስዋ ጋር እርሱንና አንድ የሦስት ዓመት ወይፈን፥ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጣችው፥ ሕፃኑም ገና ታናሽ ነበረ።