ዘኍል 11:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እግዚአብሔርን አለው፦ ለምን በባሪያህ ላይ ክፉ አደረግህ? ለምንስ በፊትህ ሞገስ አላገኘሁም? ለምንስ የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም በእኔ ላይ አደረግህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል ጠየቀው፤ “እንዲህ ያለውን መከራ በባሪያህ ላይ ለምን አመጣህ? ለምንስ በፊትህ ሞገስ አላገኘሁም? የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም የጫንህብኝስ ምን አስቀይሜህ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ጌታን እንዲህ አለው፦ “ለምን በባርያህ ላይ ክፉ አደረግህ? ለምንስ በፊትህ ሞገስ አላገኘሁም? ለምንስ የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም በእኔ ላይ አደረግህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርንም እንዲህ አለው፦ “ይህን ከባድ ነገር በእኔ በአገልጋይህ ላይ ስለምን አመጣህብኝ? ለምንስ በፊትህ ሞገስን አላገኘሁም? የዚህን ሁሉ ሕዝብስ ከባድ ኀላፊነት ለምን በእኔ ላይ ጫንከው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እግዚአብሔርን አለው፥ “ለምን በአገልጋይህ ላይ ክፉ አደረግህ? ለምንስ በፊትህ ሞገስን አላገኘሁም? ለምንስ የዚህን ሁሉ ሕዝብ ሸክም በእኔ ላይ አደረግህ? |
እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፥ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።
ስለ ምን ሕመሜ አዘወተረኝ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ፦ አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆነኛለህን?
እናንተም፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፥ ትእዛዙንስ በመጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ፊት ኀዘንተኞች ሆነን በመሄድ ምን ይረባናል?