ኢያሱ 9:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ ደግሞ ተንኰል አደረጉ፥ ለራሳቸውም ስንቅ ያዙ፥ በአህዮቻቸውም ላይ አሮጌ ዓይበትና ያረጀና የተቀደደ የተጠቀመም የጠጅ አቁማዳ ጫኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለማታለል ፈለጉ፤ ስለዚህም ያረጀ ስልቻና የተጣፈ አሮጌ የወይን ጠጅ አቍማዳ በአህያ የጫነ መልእክተኛ መስለው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ደግሞ ተንኰል አደረጉ፤ ለራሳቸውም ስንቅ ያዙ፥ በአህዮቻቸውም ላይ አሮጌ ዓይበትና ያረጀና የተቀደደ የተጠገነም የወይን ጠጅ አቁማዳ ጫኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱን ለማታለል ወሰኑ፤ እነርሱም ስንቃቸውን አዘጋጅተው፥ አሮጌ ስልቻና ቀዳዳው ተለጥፎ የተሰፋ የወይን ጠጅ አቁማዳ በአህዮች ጫኑ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ ደግሞ ተንኰል አድርገው መጡ፤ ለራሳቸውም ስንቅ ያዙ፤ በትከሻቸውም ላይ አሮጌ ዓይበትና ያረጀና የተቀደደ የተጠቀመም የጠጅ ረዋት ተሸከሙ። |
በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።
በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል የወይኑም ጠጅ ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ።
እነዚህም የጠጅ አቁማዳዎች አዲስ ሳሉ ሞላንባቸው፥ እነሆም፥ ተቀድደዋል፥ መንገዳችንም እጅግ ስለ ራቀብን እነዚህ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችን አርጅተዋል።