ኢያሱ 9:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሽማግሌዎቻችንም በምድራችንም የሚኖሩት ሁሉ፦ ለመንገድ ስንቅ በእጃችሁ ያዙ፥ ልትገናኙአቸውም ሂዱ፦ እኛ ባሪያዎቻችሁ ነን፥ አሁንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ በሉአቸው አሉን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽማግሌዎቻችንና በአገራችን የሚኖሩት ሁሉ፣ ‘ለመንገዳችሁ የሚሆን ስንቅ ያዙ፤ ሄዳችሁም ተገናኟቸው፤ “እኛ ባሮቻችሁ እንሆናለን፤ ከእኛ ጋራ ቃል ኪዳን ግቡ” በሏቸው’ አሉን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሽማግሌዎቻችንም በምድራችንም የሚኖሩት ሁሉ እንዲህ አሉን፦ ‘ለመንገድ ስንቅ በእጃችሁ ያዙ፥ ልትገናኙአቸውም ሂዱ እንዲህም በሉአቸው፦ “እኛ ባርያዎቻችሁ ነን፤ እንግዲህ አሁን ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ።” ’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሪዎቻችንና በምድራችን የሚኖሩት ሕዝቦች ሁሉ ለመንገዳችን የሚሆነንን ስንቅ አዘጋጅተን መጥተን ከእናንተ ጋር እንድንገናኝ ልከውናል፤ ለእናንተ የምንታዘዝ አገልጋዮች እንድንሆንና እናንተም ከእኛ ጋር የሰላም ውል እንድታደርጉ እንጠይቃችሁ ዘንድ አዘውናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሽማግሌዎቻችንና የሀገራችን ሰዎች ሁሉ፦ ለመንገድ ስንቅ ያዙ፤ ልትገናኙአቸውም ሂዱ፦ እኛ ባሪያዎቻችሁ ነን፤ አሁንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ በሉአቸው አሉን። |
የቤቱ አለቃ፥ የከተማይቱም አለቃ፥ ሽማግሌዎችና ልጆቹን የሚያሳድጉ “እኛ ባሪያዎችህ ነን፤ ያዘዝኸንንም ሁሉ እናደርጋለን፤ ንጉሥም በላያችን አናነግሥም፤ የምትወድደውን አድርግ፤” ብለው ወደ ኢዩ ላኩ።
የንጉሡም ትእዛዝና አዋጅ በደረሰበት አገርና ከተማ ሁሉ ለአይሁድ ደስታና ተድላ፥ የግብዣም ቀን መልካምም ቀን ሆነ። አይሁድንም መፍራት ስለ ወደቀባቸው ከምድር አሕዛብ ብዙ ሰዎች አይሁድ ሆኑ።
እንዲህም አላቸው፦ በትርም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ እንጀራም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን ለመንገድ ምንም አትያዙ፥ ሁለት እጀ ጠባብም አይሁንላችሁ።
በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል።