በአሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎምርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፤ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይ፥ ዙዚምንም በሃም፥ ኤሚምንም በሴዊ ቂርያታይም መቱ፤
ኢያሱ 9:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ከዮርዳኖስ ማዶ ባሉት በሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት ማለትም በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን፣ አስታሮትን ይገዛ በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምሥራቅ በነበሩት በሁለቱ አሞራውያን ነገሥታት ላይ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል፤ እነዚህም ሁለቱ ነገሥታት በዐስታሮት ይኖሩ የነበሩት የሐሴቦን ንጉሥ ሲሖንና የባሳን ንጉሥ ዖግ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞሬዎን ነገሥት በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን፥ በአስታሮትና በኤድራይን በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል። |
በአሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎምርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፤ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይ፥ ዙዚምንም በሃም፥ ኤሚምንም በሴዊ ቂርያታይም መቱ፤
ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፦ ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ ያገኘንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤
የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና፥ ልቡንም አጽንቶታልና።
በባሳንም ያሉት የዐግ መንግሥት ከተሞች፥ አስታሮትና ኤድራይ ነበረ። እነዚህም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ሆኑ፥ ለማኪር ልጆች እኩሌታ በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፥ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥ በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል።
ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፦ እግዚአብሔር ምድሪቱን እንደ ሰጣችሁ፥ እናንተንም መፍራት በላያችን እንደ ወደቀ፥ በምድሪቱም የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ እንደ ቀለጡ አወቅሁ።
ሽማግሌዎቻችንም በምድራችንም የሚኖሩት ሁሉ፦ ለመንገድ ስንቅ በእጃችሁ ያዙ፥ ልትገናኙአቸውም ሂዱ፦ እኛ ባሪያዎቻችሁ ነን፥ አሁንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ በሉአቸው አሉን።