አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ፥ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፦ አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁም ጊዜ ግደሉት፥ አትፍሩም፥ ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ ጽኑም ብሎ አዘዛቸው።
ኢያሱ 8:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በያዛችኋትም ጊዜ ከተማይቱን በእሳት አቃጥሉአት፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል አድርጉ፥ እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተማዪቱን ስትይዙም በእሳት አቃጥሏት፤ እግዚአብሔር ያዘዘውንም አድርጉ፤ እነሆ አዝዣችኋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በያዛችኋትም ጊዜ ከተማይቱን በእሳት አቃጥሉአት፤ እንደ ጌታ ቃል አድርጉ፤ እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተማይቱን ከያዛችሁ በኋላ፥ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በእሳት አቃጥሉአት። እነሆ፥ አዝዤአችኋለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በያዛችኋትም ጊዜ ከተማዪቱን በእሳት አቃጥሉአት፤ እንደ አልኋችሁ አድርጉ፤ እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ።” |
አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ፥ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፦ አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁም ጊዜ ግደሉት፥ አትፍሩም፥ ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ ጽኑም ብሎ አዘዛቸው።
ከተማይቱንም በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፥ ነገር ግን ብሩንና ወርቁን የናሱንና የብረቱንም ዕቃ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አደረጉት።
በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የተደበቁትን ሕዝብ አኖሩ፥ ኢያሱም በዚያች ሌሊት ወደ ሸለቆው መካከል ሄደ።
በኢያሪኮና በንጉሥዋም እንዳደረግህ እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ ታደርጋለህ፥ ምርኮዋንና ከብትዋን ግን ለራሳችሁ ትዘርፋላችሁ፥ ከከተማይቱም በስተ ኋላ ድብቅ ጦር አስቀምጥ አለው።
ሌሎቹም በላያቸው ከከተማይቱ ወጡ፥ የጋይም ሰዎች በእስራኤል መካከል ሆኑ፥ እስራኤልም ከበቡአቸው፥ አንድ እንኳ ሳይቀር ሳያመልጥም ገደሉአቸው።
ኢያሱም ሰደዳቸው፥ ወደሚደበቁበትም ስፍራ ሄዱ፥ በጋይና በቤቴል መካከልም በጋይ በምዕራብ በኩል ተቀመጡ፥ ኢያሱ ግን በዚያች ሌሊት በሕዝቡ መካከል አደረ።
ልካም ከቃዴስ ንፍታሌም የአቢኒኤምን ልጅ ባርቅን ጠርታ፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፦ ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፥ ከአንተም ጋር ከንፍታሌምና ከዛብሎን ልጆች አሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፥