La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከፋሲካውም በኋላ በነጋው የምድሪቱን ፍሬ የቂጣ እንጎቻ ቆሎም በዚያው ቀን በሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከፋሲካም በኋላ በዚያ ዕለት የምድሪቱን ፍሬ ማለት ቂጣና የተጠበሰ እሸት በሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከፋሲካውም በኋላ በማግስቱ የምድሪቱን ፍሬ እርሾ ያልገባበትን የቂጣ እንጎቻና ቆሎ በዚያው ቀን በሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በከነዓን የበቀለውን እህል መብላት የጀመሩትም በዚያን ቀን ማግስት ነበር፤ የተመገቡትም የተጠበሰ እሸትና ያለ እርሾ የተጋገረ ቂጣ ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከም​ድ​ሪ​ቱም ፍሬ ቂጣና አዲስ እህል በዚ​ያው ቀን በሉ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 5:11
7 Referencias Cruzadas  

እንጀራውንም፥ የተጠበሰውንም እሸት፥ ለምለሙንም እሸት የአምላካችሁን ቍርባን እስከምታቀርቡበት እስከዚህ ቀን ድረስ አትብሉ። ይህ በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው።


በዚህም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን ለእግዚአብሔር የቂጣ በዓል ነው፤ ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ብሉ።


እናንተ የምድሪቱን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ለእግዚአብሔር የማንሣት ቍርባን ታደርጋላችሁ።


የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፥ ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ።


በነጋውም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፥ ከዚያም በኋላ ለእስራኤል ልጆች መና አልመጣላቸውም፥ ነገር ግን በዚያው ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ።