ኢያሱ 24:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡበት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ፥ ከእናንተም ጋር ተዋጉ፥ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ፥ ምድራቸውንም ወረሳችሁ፥ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በምሥራቅ ዮርዳኖስ ወደሚኖሩት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ፤ እነርሱ ወጓችሁ፤ እኔ ግን አሳልፌ በእጃችሁ ሰጠኋቸው፤ ከፊታችሁ አጠፋኋቸው፤ እናንተም ምድራቸውን ወረሳችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡበት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ፤ ከእናንተም ጋር ተዋጉ፥ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ፥ ምድራቸውንም ወረሳችሁ፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ወደሚኖሩት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ፤ እነርሱ ተዋጉአችሁ፤ እኔ ግን በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጀኋቸው፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው፤ ምድራቸውንም ወረሳችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡት ወደ አሞሬዎናውያን ምድርም ወሰድኋችሁ፤ ከእናንተም ጋር ተዋጉ፤ ሙሴም ተዋጋቸው፤ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ፤ ምድራቸውንም ወረሳችሁ፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው። |
መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና፥ ወደ አሞራውያንም ወደ ኬጢያውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ከነዓናውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ እያቡሳውያንም ያገባሃል፤ እኔም አጠፋቸዋለሁ።
እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብርታቱም እንደ ኮምበል ዛፍ የነበረውን አሞራዊውን ከፊታቸው አጠፋሁ፥ ፍሬውንም ከላዩ፥ ሥሩንም ከታቹ አጠፋሁ።