La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 2:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርስዋም፦ እንደ ቃላችሁ ይሁን አለች፥ ሰደደቻቸውም እነርሱም ሄዱ፥ ቀዩንም ፈትል በመስኮቱ በኩል አንጠለጠለችው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሷም፣ “ይሁን፤ ባላችሁት ተስማምቻለሁ” ስትል መለሰች። ከዚያም ሰደደቻቸው፤ እነርሱም ሄዱ፤ ቀይ ፈትሉንም በመስኮቷ ላይ አንጠለጠለችው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሷም እንዲህ አለች፦ “እንደ ቃላችሁ ይሁን፤” ከዚያም በኋላ በደኅና አሰናበተቻቸው እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ፈትል በመስኮቱ በኩል አንጠለጠለችው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርስዋም በዚህ ተስማምታ ሸኘቻቸው፤ እነርሱም ከሄዱ በኋላ ቀዩን ገመድ በመስኮቱ ላይ አንጠለጠለች።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ስ​ዋም፥ “እንደ ቃላ​ችሁ ይሁን” አለች፤ አሰ​ና​በ​ተ​ቻ​ቸ​ውም፤ እነ​ር​ሱም ሄዱ፤ ቀዩ​ንም ፈትል በመ​ስ​ኮቱ በኩል አን​ጠ​ለ​ጠ​ለ​ችው።

Ver Capítulo



ኢያሱ 2:21
6 Referencias Cruzadas  

የእስራኤልም ልጆች ሄዱ፤ እንዲሁም አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉ።


ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።


እናቱም ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።


እነሆ፥ እኛ ወደ አገሩ በገባን ጊዜ ይህን ቀይ ፈትል እኛን ባወረድሽበት መስኮት በኩል እሰሪው፥ አባትሽንም እናትሽንም ወንድሞችሽንም የአባትሽንም ቤተ ሰብ ሁሉ ወደ አንቺ ወደ ቤትሽ ሰብስቢ።


ይህንን ነገራችንን ግን ብትገልጪ ከዚህ ካማልሽን መሐላ ንጹሐን እንሆናለን።


እነርሱም ሄደው ወደ ተራራው ደረሱ፥ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ ሦስት ቀን በዚያ ተቀመጡ፥ አሳዳጆቹም በመንገዱ ሁሉ ፈልገው አላገኙአቸውም።