ግዛታቸውና ማደሪያቸው ቤቴልና መንደሮችዋ፥ በምሥራቅም በኩል ነዓራን፥ በምዕራብም በኩል ጌዝርና መንደሮችዋ፥ ደግሞ ሴኬምና መንደሮችዋ እስከ ጋዛና እስከ መንደሮችዋ ድረስ፥
ኢያሱ 16:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኢያኖክም ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ወረደ፥ ወደ ኢያሪኮም ደረሰ፥ ወደ ዮርዳኖስም ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኢያኖክም በመነሣት ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ቍልቍል ይወርድና በኢያሪኮ በኩል አድርጎ ዮርዳኖስ ላይ ብቅ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኢያኖክም ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ወረደ፤ ወደ ኢያሪኮም ደረሰ፥ መጨረሻውም ዮርዳኖስ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከያኖሐም ተነሥቶ ወደ ዐጣሮትና ወደ ናዓራት በመዘቅዘቅ ኢያሪኮ ደርሶ መመለሻው የዮርዳኖስ ወንዝ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኢያኖክም ወደ መአኮና፥ ወደ አጣሮትም፥ ወደ መንደሮቻቸውም ያልፋል፤ ወደ ኢያሪኮም ይገባል፥ ወደ ዮርዳኖስም ይወጣል። |
ግዛታቸውና ማደሪያቸው ቤቴልና መንደሮችዋ፥ በምሥራቅም በኩል ነዓራን፥ በምዕራብም በኩል ጌዝርና መንደሮችዋ፥ ደግሞ ሴኬምና መንደሮችዋ እስከ ጋዛና እስከ መንደሮችዋ ድረስ፥
ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፥ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ በአንድ ክምር ተነሣ፥ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፥ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ።
በዚያን ጊዜም ኢያሱ፦ ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ርጉም ይሁን፥ መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይጥፋ፥ በርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይጥፋ ብሎ ማለ።