ኢያሱ 16:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኤፍሬምም ልጆች ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፥ በምሥራቅ በኩል የርስታቸው ድንበር አጣሮትአዳር እስከ ላይኛው ቤትሖሮን ድረስ ነበረ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለኤፍሬም ወገን በየጐሣ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ድርሻ ይህ ነው፤ ድንበሩ በምሥራቅ በኩል ከአጣሮት አዳር ተነሥቶ እስከ ላይኛው ቤትሖሮን ይወጣና፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤፍሬምም ልጆች ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፤ በምሥራቅ በኩል የርስታቸው ድንበር አጣሮትአዳር እስከ ላይኛው ቤትሖሮን ድረስ ነበረ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤፍሬም ነገድ የርስት ድርሻ በየወገናቸው ይህ ነው፤ ድንበራቸው ከዐጣሮትአዳር በምሥራቅ በኩል ወደ ላይኛው ቤትሖሮን ይወጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤፍሬምም ልጆች ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፤ የርስታቸው ድንበር ከአጣሮትና፥ ከኤሮሕ ምሥራቅ ከጋዛራ እስከ ላይኛው ቤቶሮን ድረስ ነበረ፤ |
ግዛታቸውና ማደሪያቸው ቤቴልና መንደሮችዋ፥ በምሥራቅም በኩል ነዓራን፥ በምዕራብም በኩል ጌዝርና መንደሮችዋ፥ ደግሞ ሴኬምና መንደሮችዋ እስከ ጋዛና እስከ መንደሮችዋ ድረስ፥
እግዚአብሔርም በእስራኤል ፊት አስደነገጣቸው፥ በገባዖንም ታላቅ መምታት መታቸው፥ በቤትሖሮንም ዐቀበት በመንገድ አሳደዳቸው፥ እስከ ዓዜቃና እስከ መቄዳ ድረስ መታቸው።
ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ አለፈ፥ ድንበሩም በታችኛው ቤትሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮትአዳር ወረደ።