ባሳንንም ሁሉ እስከ ሰልካ ድረስ፥ በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፥ እርሱም ከራፋይም የቀረ ነበረ፥ እነዚህንም ሙሴ መታቸው አወጣቸውም።
ኢያሱ 12:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከራፋይምም ወገን የቀረ፥ በአስታሮትና በኤድራይ የተቀመጠው፥ የአርሞንዔምንም ተራራ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መቀመጫውን በአስታሮትና በኤድራይ አድርጎ የገዛውና ከመጨረሻዎቹ ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነው የባሳን ንጉሥ ዐግ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከራፋይምም ወገን የቀረ፥ በአስታሮትና በኤድራይ የተቀመጠው የባሳን ንጉሥ ዐግ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ከረፋያውያን ወገን የቀረው በአስታሮትና በኤድራይ ይኖር የነበረው የባሳን ንጉሥ ዖግ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከረዓይት ወገን የቀረ፥ በአስጣሮትና በኤንድራይን የተቀመጠው፥ |
ባሳንንም ሁሉ እስከ ሰልካ ድረስ፥ በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፥ እርሱም ከራፋይም የቀረ ነበረ፥ እነዚህንም ሙሴ መታቸው አወጣቸውም።
በባሳንም ያሉት የዐግ መንግሥት ከተሞች፥ አስታሮትና ኤድራይ ነበረ። እነዚህም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ሆኑ፥ ለማኪር ልጆች እኩሌታ በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።