ኢያሱ 11:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ ፈጽመውም አጠፉአቸው፥ እስትንፋስ ያለውንም አላስቀሩም፥ አሶርንም በእሳት አቃጠላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በውስጧ ያሉትን ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እስትንፋስ ካለው ፍጡር አንድ እንኳ ሳያስቀሩ ሁሉንም ደመሰሱ፤ ራሷን አሦርንም በእሳት አቃጠሏት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ ፈጽመውም አጠፉአቸው፤ እስትንፋስ ያለውንም አላስቀሩም፤ አሦርንም በእሳት አቃጠላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን በሐጾር የተገኘውን ሰው ሁሉ ስለ ገደሉ በሕይወት የተረፈ አልነበረም፤ ከተማይቱም በእሳት ተቃጠለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርስዋም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ገደሉ፤ እስትንፋስ ያላቸውንም ሁሉ ሳያስቀሩ ሁሉንም አጠፉአቸው፤ አሶርንም በእሳት አቃጠላት፤ |
አምላክህ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸው በመታሃቸውም ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፤ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፥ አትማራቸውም፤
እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ተራራማውን አገር ደቡቡንም ቈላውንም ቁልቁለቱንም ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ መታ፥ ማንንም አላስቀረም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ነፍስ ያለበትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
ከተማይቱንም በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፥ ነገር ግን ብሩንና ወርቁን የናሱንና የብረቱንም ዕቃ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አደረጉት።