ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን በዙሪያ መንገድ በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ምድር ተሰልፈው ወጡ።
ኢያሱ 1:14 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ ከብቶቻችሁም ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቀመጡ፥ ነገር ግን እናንተ፥ ጽኑዓን ኃያላን ሁሉ፥ ተሰልፋችሁ በወንድሞቻችሁ ፊት ተሻገሩ፥ እርዱአቸውም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ እንዲሁም ከብቶቻችሁ ሙሴ በሰጣችሁ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ባለው ምድር ይቈዩ፤ ነገር ግን ተዋጊዎቻችሁ ሁሉ፣ ከነሙሉ ትጥቃቸው፣ ከወንድሞቻችሁ ቀድመው ይሻገሩ፤ እናንተም ከወንድሞቻችሁ ጐን ተሰለፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ ከብቶቻችሁም ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቀመጡ፤ ነገር ግን እናንተ፥ ጽኑዓን ኃያላን ሁሉ፥ ተሰልፋችሁ በወንድሞቻችሁ ፊት ተሻገሩ፥ እርዱአቸውም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ሙሴ ከዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቈዩ፤ የጦር ልብስ ለብሰው ለውጊያ የተዘጋጁ ሰዎቻችሁ ግን ወገኖቻቸውን እስራኤላውያንን ለመርዳት ግንባር ቀደም ሆነው ዮርዳኖስን ይሻገሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ ከብቶቻችሁም ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ በዚች ምድር ይቀመጡ፤ እናንተ፥ ጽኑዓን ሁሉ ግን ታጥቃችሁ በወንድሞቻችሁ ፊት ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ ለእነርሱም ተዋጉላቸው። |
ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን በዙሪያ መንገድ በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ምድር ተሰልፈው ወጡ።
አለቆቹም ደግሞ ጨምረው፦ ማንም ፈሪና ድንጉጥ ሰው ቢሆን እርሱ ፈርቶ የወንድሞቹን ልብ ደግሞ እንዳያስፈራ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ ብለው ለሕዝቡ ይናገሩ።
በዚያ የአለቃ እድል ፈንታ ቀርቶአልና 2 የመጀመሪያውን ክፍል ለራሱ መረጠ፤ 2 ወደ ሕዝብ አለቆችም መጣ፤ 2 የእግዚአብሔርንም ጽድቅ፥ 2 ፍርዱንም ከእስራኤል ጋር አደረገ።
እግዚአብሔር እናንተን እንዳሳረፋችሁ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ፥ እነርሱም ደግሞ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ፥ ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በፀሐይ መውጫ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ትመለሳላችሁ ትወርሱአትማላችሁ።
ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፥ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤