ሥራህንም የምታውቅ ጥበብ ከአንተ ጋር ነበረች፤ ዓለምንም በፈጠርኽ ጊዜ ነበረች፤ በፊትህ ደስ የሚያሰኝህም ምን እንደ ሆነ፥ ለትእዛዝህም የቀናው ምን እንደ ሆነ ትረዳ ነበር።
ዓለምን በፈጠርህ ጊዜ ከጐንህ ያልተለየችው፥ ሥራዎችህን የምታውቀው ጥበብ ካንተ ጋር ናት። አንተን ደስ የሚያሰኘውን፥ ከትእዛዞችህ ጋር የሚስማማውን ሁሉ ታውቃለች።