ያም ባይሆን በየወገኖቻቸው እንዲማርኳቸው ክፉዎችን በጻድቃን እጅ ትጥላቸው ዘንድ አይሳንህም ነበር፥ ያም ባይሆን ለክፉዎች አውሬዎች ትሰጣቸው ዘንድ፥ ያም ባይሆን በአንድ ቃል አዝዘህ ታጠፋቸው ዘንድ አይሳንህም ነበር።
በተፋፋመ ጦርነት መሀል ክፉዎችን በጻድቃኖች እጅ መጣል ችግርህ አልነበረም፤ ወይንም እነርሱን በአስፈሪ አውሬዎች አልያም በቁጣ ቃል ልታጠፋቸውም በቻልህ ነበር፤