አማልክት እንደ ሆኑ ባሰቧቸው በእነዚህ በጣዖታቱ በተፈረደባቸው ጊዜ ቀድሞ የካዱትን ያውቁታል፥ ጻድቅ አምላክ እንደ ሆነም ያውቁታል፤ ስለዚህም ፍጹም የፍርድ ቅጣት ደረሰባቸው።
እነርሱን ያሰቃያቸው፥ አቤቱታቸውን ያቀረቡባቸው፥ አምላኮቻቸው ያደረጉአቸው እነኛው ፍጡራን፥ የቀጧቸውም እነርሱ መሆናቸውን በእውነተኛው ብርሃናቸው ተመልክተዋል፤ እስከ አሁን ድረስ አናውቅህም ያሉትን ጌታ እውነተኛው አምላክ እንደሆነ አወቁ፤ የመጨረሻውም ቅጣት በእነርሱ ላይ ወደቀ።