ለእነዚህ የንስሓ ቦታ ሰጥተህ ይህ ጥቂት በጥቂት ይሆን ዘንድ ፈረድህ፤ ይህንም ማድረግህ አኗኗራቸው ክፉ እንደ ሆነ፥ ክፋታቸውም እጅግ እንደ በዛ፥ ዐሳባቸውም ለዘለዓለም እንደማይመለስ ሳታውቅ አይደለም።
ምንም እንኳ እነርሱ በክፋት የተጠነሰሱ መሆናቸውን ብታውቅም፥ በተፈጥሮአቸው ክፉዎች ቢሆኑም፥