አንተ ሁሉን የምትችል ነህና ሁሉን ይቅር ትላለህ፥ ለንስሓም እየጠበቅኸው የሰውን ኀጢአት ቸል ትላለህ።
ፍጥረቶችህን ሁሉ ትወዳለህ፤ ከፍጡራንህ አንዱን ስንኳ አትጠላም፤ ምክንያቱም ብትጠላው ኖሮ አትፈጥረውምና።