አወን አቤቱ የአባቴ አምላክ፥ የእስራኤልም የርስታቸው አምላክ፥ የሰማይና የምድር አምላክ፥ ውኃውን የፈጠርህ፥ የፍጥረታት ሁሉ ንጉሥ አንተ ጸሎቴን ስማ።
የአባቴ አምላክ፥ የእስራኤል ርስት፥ የሰማይና የምድር ጌታ፥ የውኆች ፈጣሪ፥ የፍጡራን ሁሉ ንጉሥ ሆይ፥ እባክህን እባክህን ጸሎቴን ስማኝ!