ፍጥረትህ ሁሉ ለአንተ ይገዛሉ፤ አንተ አዘዝህ፤ እነርሱም ተፈጥረዋልና፤ መንፈስህን ላክህ፤ እነርሱም ታነጹ፥ ለቃልህም የማይታዘዝ የለም።
በወገኖቼ ላይ የሚነሡ አሕዛብ ወዮላቸው፤ ሁሉን የሚችል ጌታ በፍርድ ቀን ይበቀላቸዋል፤ በሥጋቸውም ላይ እሳትንና ትልን ያመጣባቸዋል፤ በስቃይም ለዘለዓለም ያለቅሳሉ።”