ያንጊዜ የተጨነቁ ወገኖች ደስ ብሏቸው ደነፉ፤ የእኔ ደካሞች በታላቅ ድምፅ ጮኹ፤ እነዚያም ደንግጠው ነበር፤ እነዚህም ድምፃቸውን ከፍ ከፍ አደረጉ፤ እነዚያም ደንግጠው ሸሹ፤
ለአምላኬ አዲስ የምስጋናን መዝሙር እዘምራለሁ፤ ጌታ ሆይ አንተ ትልቅና ክቡር፥ በብርታትህ የምትደነቅና የማትሸንፍ ነህ።