ጫማዎችዋም ዐይኖቹን በዘበዙ፤ ደም ግባትዋም ሰውነቱን ማረከች፤ ሰይፍም በአንገቱ አለፈ።
በዚያን ጊዜ የእኔ ትሑታን ጮኹ፥ የእኔ ደካሞች በጣም ጮኹ፤ እነዚያም በድንጋጤ ተዋጡ፤ የእኔ ሰዎች ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፥ እነዚያም ደንግጠው ሸሹ።