ከዚህ በኋላ ሲነጋ ፀሐይ በወጣ ጊዜ ሁላችሁም የጦር መሣሪያችሁን ያዙ፤ አርበኞች የሆኑ ሰዎች ሁሉ ከከተማ ወደ ውጭ ይውጡ፤ የአሦራውያን ሠራዊት ጠባቂዎችም ወዳሉበት ቦታ እንደምትወርዱ ሆናችሁ አለቃ ለራሳችሁ ሹሙ። ነገር ግን አትውረዱ።
ጧት ሲነጋና በምድር ላር ፀሐይ ስትወጣ ሁላችሁም የጦር መሣሪያችሁን ያዙ፤ ለጦር የደረሱ ወንዶች ሁሉ ከከተማይቱ ይውጡ፤ አንድ አለቃ ሹሙ፥ ወደ አሦራውያን ሜዳው የጥበቃ ኬላ የምትወርዱ ምሰሉ፤ ነገር ግን አትውረዱ።