ሆሎፎርኒስም አላት፥ “አንቺ ሴት እመኝ፤ ለዓለሙ ሁሉ ንጉሥ ለናቡከደነፆር ይገዛ ዘንድ ራሱን ወደ እርሱ በመለሰ ሰው እኔ ክፉ ነገርን አላደርግምና ልቡናሽ አይፍራብሽ።
ሆሎፎርኒስም እንዲህ አላት፦ “አንቺ ሴት አይዞሽ፥ ልብሽም አይፍራ፥ የምድር ሁሉ ገዢ የሆነውን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ለማገልገል የቆረጠን ሰው ጉዳት አድርሼ አላውቅምና።