የወይኑን ገንቦና የዘይቱን ማሰሮ ትሸከም ዘንድ ለብላቴናዋ ሰጠቻት፤ ስልቅ በሶውን፥ የስንዴ አምባሻውንና በለሱን በስልቻዋ መላች፤ ገንዘብዋንም ሁሉ አንግታ አሸከመቻት።
አገልጋይዋን የወይን አቁማዳ፥ የዘይት ማሰሮ አስያዘቻት፤ በከረጢት ውስጥ በሶና የደረቅ በለስ ፍሬ፤ ቂጣ ሞላች፤ ዕቃዎቿን ሁሉ በደንብ ጠቀለለችና አገልጋይዋን አሸከመቻት።