መጽሐፈ ዮዲት 10:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የለበሰችውንም ማቅ አወለቀች፤ የመበለትነትዋንም ልብስ ለበሰች፥ ሰውነትዋንም በውኃ ታጠበች፤ ጠጕርዋንም ያማረ ሽቱ ተቀባች፤ ጠጕርዋንም ተሠራች፤ አጌጠችም፤ ከዚህም በኋላ ባሏ ምናሴ በሕይወት በነበረ ጊዜ የምትለብሰውን የደስታ ልብሷን ለበሰች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የለበሰችውን ማቅ አወለቀች፤ የመበለትነት ልብስዋን ተወች፥ ሰውነትዋንም በውኃ ታጠበች፥ ጥሩ ሽቶ ተቀባች፤ ጠጉርዋን አበጠረች፥ በራስዋም ላይ ሻሽ አደረገች፤ ባሏ ምናሴ በሕይወት በነበረበት ጊዜ ትለብሰው የነበረውን የደስታ ልብስዋን ለበሰች። |