መሳፍንት 9:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር ያሉትም ሕዝብ ሁሉ ወደ ሄርሞን ተራራ ወጡ፤ አቤሜሌክም በእጁ መጥረቢያ ወስዶ የዛፉን ቅርንጫፍ ቈረጠ፤ አንሥቶም በጫንቃው ላይ ተሸከመው፤ ከእርሱም ጋር ለነበሩት ሕዝብ፥ “እኔ ሳደርግ ያያችሁትን፥ እናንተም ፈጥናችሁ እኔ እንዳደረግሁ አድርጉ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱና ሰዎቹ ሁሉ ወደ ሰልሞን ተራራ ወጡ፤ አቢሜሌክም መጥረቢያ ወስዶ ጥቂት የዛፍ ቅርንጫፍ ቈረጠ፤ በትከሻውም ላይ አደረገ። የተከተሉትንም ሰዎች፣ “ፍጠኑ፤ እኔ ሳደርግ ያያችሁትን አድርጉ” ሲል አዘዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱና ሰዎቹ ሁሉ ወደ ሰልሞን ተራራ ወጡ፤ አቤሜሌክም መጥረቢያ ወስዶ ጥቂት የዛፍ ቅርንጫፍ ቈረጠ፤ በትከሻውምላይ አደረገ። የተከተሉትንም ሰዎች፥ “ፍጠኑ፤ እኔ ሳደርግ ያያችሁትን አድርጉ” ሲል አዘዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ከተከታዮቹ ጋር ወደ ጻልሞን ተራራ ወጣ፤ ከዚያም መጥረቢያ ወስዶ ከዛፍ ላይ እንጨት በመቊረጥ በትከሻው ተሸከመ፤ ተከታዮቹም በፍጥነት እርሱ እንዳደረገው ያደርጉ ዘንድ ነገራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር ያሉትም ሕዝብ ሁሉ ወደ ሰልሞን ተራራ ወጡ፥ አቤሜሌክም በእጁ መጥረቢያ ወስዶ የዛፉን ቅርንጫፍ ቈረጠ፥ አንሥቶም በጫንቃው ላይ አደረገው፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት ሕዝብ፦ እኔ ሳደርግ ያያችሁትን፥ እናንተም ፈጥናችሁ እኔ እንዳደረግሁ አድርጉ አላቸው። |
ሕዝቡም ሁሉ እንዲሁ እያንዳንዳቸው የዛፉን ቅርንጫፎች ቈረጡ፤ አቤሜሌክንም ተከትለው በምሽጉ ዙሪያ አኖሩአቸው፤ ምሽጉንም በላያቸው በእሳት አቃጠሉት፤ የሰቂማም ግንብ ሰዎች ሁሉ ደግሞ አንድ ሺህ የሚያህሉ ወንድና ሴት ሞቱ።