መሳፍንት 9:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሜሌክም በዚያ ቀን ሁሉ ከከተማዪቱ ጋር ተዋጋ፤ ከተማዪቱንም ይዞ በእርስዋ የነበሩትን ሕዝብ ገደለ፤ ከተማዪቱንም አፈረሰ፤ ጨውም ዘራባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ዕለት አቢሜሌክ ቀኑን ሙሉ ከተማዪቱን ሲወጋ ውሎ በመጨረሻ ያዛት፤ ሕዝቧን ፈጀ፤ ከተማዪቱንም አጠፋ፤ በላይዋም ጨው ዘራባት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ዕለት አቤሜሌክ ቀኑን ሙሉ ከተማይቱን ሲወጋ ውሎ በመጨረሻ ያዛት፤ ሕዝቧን ፈጀ፤ ከተማይቱንም አጠፋ፤ በላይዋም ጨው ዘራባት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውጊያውም ቀኑን ሙሉ ቀጥሎ ዋለ፤ አቤሜሌክ ከተማይቱን ይዞ ሕዝብዋን ሁሉ ገደለ፤ ከተማይቱን አፈራረሰ፤ በምድሪቱም ላይ ጨው ዘራባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሜሌክም በዚያ ቀን ሁሉ ከከተማይቱ ጋር ተዋጋ፥ ከተማይቱንም ይዞ በእርሷ የነበሩትን ሕዝብ ገደለ፥ ከተማይቱንም አፈረሰ፥ ጨውም ዘራባት። |
ከተሞቻቸውንም አፈረሱ፤ በመልካሞቹም እርሻዎቻቸው ሁሉ ላይ እስኪሞሉ ድረስ እያንዳንዱ ሰው አንድ አንድ ድንጋይ ይጥል ነበር፤ የውኃውንም ምንጮች ሁሉ ደፈኑ፤ የከተሞቻቸውንም ቅጥር አፈረሱ፤ የሚያምሩትን ዛፎች ሁሉ ቈረጡ፤ ባለ ወንጭፎችም ከብበው መቱአቸው።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በእርግጥ ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ፥ የሳማ ስፍራና የጨው ጕድጓድ ለዘላለምም ምድረ በዳ ሆነው ይኖራሉ፣ የሕዝቤም ቅሬታ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።
ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ መቃጠልም እንደ ሆነባት፥ እንዳይዘራባትም፥ እንዳታበቅልም፥ ማናቸውም ሣርና ልምላሜም እንዳይወጣባት፥ እግዚአብሔር በቍጣውና በመዓቱ እንደ ገለበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥
አቤሜሌክም ከእርሱም ጋር ያሉት ሠራዊት በከተማዪቱ መግቢያ በር ሸምቀው ቆሙ። እነዚያ ሁለቱ ሠራዊት ግን ወደ ጫካው ተበትነው አጠፉአቸው።