ምርኮን ትማርክ ዘንድ፥ ብዝበዛንም ትበዘብዝ ዘንድ፥ ባድማም በነበሩ፥ አሁንም ሰዎች በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ላይ፥ ከአሕዛብም በተሰበሰበ፥ ከብትና ዕቃንም በአገኘ፥ በምድርም መካከል በተቀመጠ ሕዝብ ላይ እጅህን ትመልሳለህ።
መሳፍንት 9:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገዓልም ደግሞ፥ “እነሆ፥ ሕዝብ በባሕር በኩል ወደ ምድር መካከል ይወርዳል፤ የአንድም አለቃ ሠራዊት በአድባሩ ዛፍ መንገድ አንጻር ይመጣል” ብሎ ተናገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገዓልም፣ “ተመልከት እንጂ ሕዝብ እኮ ከተራራው ወገብ ላይ እየደረሰ ነው፤ አንዱ ክፍልም በቃላተኞች ዛፍ በኩል አድርጎ እየመጣ ነው” ብሎ እንደ ገና ተናገረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገዓልም፥ “ተመልከት እንጂ ሕዝብ እኮ ከተራራው ወገብ ላይ እየደረሰ ነው፤ አንዱ ክፍልም በአስማተኞች የባሉጥ ዛፍ በኩል አድርጎ እየመጣ ነው” ብሎ እንደገና ተናገረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ጋዓል “ተመልከት! ከከፍተኛ ቦታ መካከል ሰዎች ቊልቊል በመውረድ ላይ ናቸው፤ አንዱ ቡድን የአስማተኞች የወርካ ዛፍ በሚባለው መንገድ እየመጣ ነው!” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገዓልም ደግሞ፦ እነሆ፥ ሕዝብ በምድር መካከል ይወርዳል፥ አንድም ወገን በምዖንኒም በአድባሩ ዛፍ መንገድ ይመጣል ብሎ ተናገረ። |
ምርኮን ትማርክ ዘንድ፥ ብዝበዛንም ትበዘብዝ ዘንድ፥ ባድማም በነበሩ፥ አሁንም ሰዎች በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ላይ፥ ከአሕዛብም በተሰበሰበ፥ ከብትና ዕቃንም በአገኘ፥ በምድርም መካከል በተቀመጠ ሕዝብ ላይ እጅህን ትመልሳለህ።
አንተ የምትወርሳቸው እነዚህ አሕዛብ ሞራ ገላጮችንና ምዋርተኞችን ያዳምጣሉ፤ ለአንተ ግን እንዲህ አይደለም፤ አምላክህ እግዚአብሔር አልፈቀደምና።
የአቤድ ልጅ ገዓልም ሕዝቡን ባየ ጊዜ ዜቡልን፥ “እነሆ፥ ከተራሮች ራስ ሕዝብ ይወርዳል” አለው። ዜቡልም፥ “ሰዎችን የሚመስለውን የተራሮችን ጥላ ታያለህ” አለው።
ዜቡልም፥ “እንገዛለት ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው? ያልህበት አፍህ አሁን የት አለ? ይህ የናቅኸው ሕዝብ አይደለምን? አሁንም ወጥተህ ከእነርሱ ጋር ተዋጋ” አለው።