መሳፍንት 9:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአቤድ ልጅ ገዓልም ሕዝቡን ባየ ጊዜ ዜቡልን፥ “እነሆ፥ ከተራሮች ራስ ሕዝብ ይወርዳል” አለው። ዜቡልም፥ “ሰዎችን የሚመስለውን የተራሮችን ጥላ ታያለህ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገዓል ባያቸው ጊዜ ዜቡልን፣ “ተመልከት፤ ከተራራው ጫፍ ሕዝብ እየወረደ ነው” አለው። ዜቡልም መልሶ፣ “የተራሮች ጥላ ሰዎች መስሎ ተሳስተህ” ነው አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገዓል ባያቸው ጊዜ ዜቡልን፥ “ተመልከት፤ ከተራራው ጫፍ ሕዝብ እየወረደ ነው” አለው። ዜቡልም መልሶ፥ “የተራሮች ጥላ ሰዎች መስሎ ተሳስተህ ነው” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጋዓልም እነርሱን አይቶ ዘቡልን “ተመልከት! ሰዎች ከተራራው ጫፍ ላይ እየወረዱ ነው!” አለው። ዘቡልም “እነርሱ በተራሮች ላይ የሚታዩ ጥላዎች እንጂ ሰዎች አይደሉም” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገዓልም ሕዝቡን ባየ ጊዜ ዜቡልን፦ እነሆ፥ ከተራሮች ራስ ሕዝብ ይወርዳል አለው። ዜቡልም፦ ሰዎች የሚመስለውን የተራሮችን ጥላ ታያለህ አለው። |
በነጋም ጊዜ የአቤድ ልጅ ገዓል ወጥቶ በከተማዪቱ መግቢያ በር ቆመ፤ አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር ያሉት ሕዝብም ከሸመቁበት ስፍራ ተነሡ።
ገዓልም ደግሞ፥ “እነሆ፥ ሕዝብ በባሕር በኩል ወደ ምድር መካከል ይወርዳል፤ የአንድም አለቃ ሠራዊት በአድባሩ ዛፍ መንገድ አንጻር ይመጣል” ብሎ ተናገረ።