አቤሴሎምም፥ “ነገርና ክርክር ያለው ሁሉ ወደ እኔ ይመጣ ዘንድ፥ ቅንም ፍርድ እፈርድለት ዘንድ በሀገር ላይ ፈራጅ አድርጎ ማን በሾመኝ?” ይል ነበር።
መሳፍንት 9:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ ሕዝብ ከእጄ በታች ቢሆን ኖሮ አቤሜሌክን አሳድደው ነበር” አለ። አቤሜሌክንም፥ “ሠራዊትህን አብዝተህ ና፤ ውጣ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምነው ይህን ሕዝብ የማዝዘው እኔ በሆንሁ ኖሮ! አቢሜሌክን አስወግደው ነበር፤ ‘ሰራዊትህን አብዝተህ ውጣ!’ እለው ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምነው ይህን ሕዝብ የማዘው እኔ በሆንሁ ኖሮ፥ አቤሜሌክን አስወግደው ነበር፤ ‘ሠራዊትህን አብዝተህ እስቲ ውጣ! እለው ነበር።’” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ሕዝብ የምመራው እኔ በሆንኩ ኖሮ! አቤሜሌክን ወዲያ አስወግደው ነበር፤ ደግሞም ‘ሠራዊትህን በማጠንከር ወጥተህ ተዋጋ!’ ብዬ እነግረው ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ምንስ ለዚህ እንገዛለን? ይህ ሕዝብ ከእጄ በታች ቢሆን ኖሮ አቤሜሌክን አሳድደው ነበር አለ። አቤሜሌክንም፦ ሠራዊትህን አብዝተህ ና፥ ውጣ አለው። |
አቤሴሎምም፥ “ነገርና ክርክር ያለው ሁሉ ወደ እኔ ይመጣ ዘንድ፥ ቅንም ፍርድ እፈርድለት ዘንድ በሀገር ላይ ፈራጅ አድርጎ ማን በሾመኝ?” ይል ነበር።
በከተማውም የተቀመጡት የከተማው ሰዎችና ሽማግሌዎች፥ አለቆችም ኤልዛቤል እንዳዘዘቻቸውና ወደ እነርሱ በተላከው ደብዳቤ እንደ ተጻፈው እንዲሁ አደረጉ።
በዚያን ጊዜም አሜስያስ፥ “ና እርስ በርሳችን ፊት ለፊት እንተያይ” ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ዮአስ መልእክተኞችን ላከ።
አሁንም እንግዲህ ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ ጋር ተወራረድ፤ የሚቀመጡባቸውንም ሰዎች ማግኘት ቢቻልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረሶች እሰጥሃለሁ።