መሳፍንት 8:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድያምም በእስራኤል ልጆች ተዋረዱ፤ ራሳቸውንም ዳግመኛ አላነሡም፤ በጌዴዎንም ዕድሜ ምድሪቱ አርባ ዓመት ዐረፈች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ምድያማውያን በእስራኤላውያን ተሸነፉ፤ ዳግመኛም ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም። ጌዴዎን በሕይወት እስካለ ጊዜ ድረስ ምድሪቱ አርባ ዓመት ሰላም አገኘች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ምድያማውያን በእስራኤላውያን ተሸነፉ፤ ዳግመኛም ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም። ጌዴዎን በሕይወት እስካለ ጊዜ ድረስ ምድሪቱ አርባ ዓመት ሰላም አገኘች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት ምድያም በእስራኤላውያን ተሸነፈች፤ ዳግመኛም ለእስራኤላውያን የምታሰጋ አልሆነችም፤ ጌዴዎን እስከ ሞተም ድረስ በምድሪቱ ላይ አርባ ዓመት ሙሉ ሰላም ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድያምም በእስራኤል ልጆች ተዋረደ፥ ራሳቸውንም ዳግመኛ አላነሡም፥ በጌዴዎንም ዕድሜ ምድሪቱ አርባ ዓመት ዐረፈች። |
እግዚአብሔርም ምድያምን በመከራው ቦታ እንደ መታው ጅራፍን ያነሣበታል፤ ቍጣውም በባሕሩ መንገድና በግብፅ መንገድ በኩል ይሆናል።
በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ በላያቸው የነበረው ቀንበር ተነሥቶአልና፥ በጫንቃቸው የነበረውንም፥ የአስጨናቂዎችንም በትር መልሶአልና።
አቤቱ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፤ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኀይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፤ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።
ጌዴዎንም ምስል አድርጎ ሠራው፤ በከተማውም በኤፍራታ አኖረው፤ እስራኤልም ሁሉ ተከትሎ አመነዘረበት፤ ለጌዴዎንና ለቤቱም ወጥመድ ሆነ።
እግዚአብሔርም ፍልስጥኤማውያንን አዋረዳቸው፤ ዳግመኛም ከዚያ ወዲያ ወደ እስራኤል ድንበር አልወጡም፤ በሳሙኤልም ዘመን ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ነበረች።