መሳፍንት 6:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌዴዎንም እግዚአብሔርን፥ “እንደ ተናገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ ታድን እንደ ሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “በተናገርኸው መሠረት እስራኤላውያንን በእጄ የምታድናቸው ከሆነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “በተናገርኸው መሠረት እስራኤላውያንን በእጄ የምታድናቸው ከሆነ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፦ “እንደ ተናገርከው እስራኤልን በእኔ እጅ ታድን ዘንድ መርጠኸኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌዴዎንም እግዚአብሔርን፦ እንደ ተናገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ ታድን እንደ ሆነ፥ እነሆ፥ በአውድማው ላይ የተባዘተ የበግ ጠጉር አኖራለሁ፥ በጠጉሩ ብቻ ላይ ጠል ቢሆን በምድሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን፥ እንደ ተናገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ እንድታድናቸው አውቃለሁ አለ። |
ኢሳይያስም፥ “እግዚአብሔር የተናገረውን ነገር እንዲፈጽመው ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክቱ ይህ ይሆንልሃል፤ ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት ይሂድን? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላው ይመለስ?” አለ።
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ እርሱ ተመለከተና፥ “በዚህ በጕልበትህ ሂድ፤ እስራኤልንም ከምድያም እጅ ታድናቸዋለህ፤ እነሆ፥ ልኬሃለሁ” አለው።
የእግዚአብሔርም መልአክ፥ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ ምድያምንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ታጠፋለህ” አለው።
እነሆ! በዐውድማዉ ላይ የተባዘተ የበግ ጠጕር አኖራለሁ፤ በጠጕሩ ብቻ ላይ ጠል ቢሆን በምድሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን፥ እንደ ተናገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ እንደምታድናቸው አውቃለሁ” አለ።
ነገር ግን ወደ እኛ ውጡ ቢሉን እግዚአብሔር በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና እንወጣለን፤ ምልክታችንም ይህ ይሆናል።”