መሳፍንት 6:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስ በርሳቸውም፥ “ይህን ነገር ያደረገ ማን ነው?” ተባባሉ። በጠየቁና በመረመሩም ጊዜ፥ “ይህን ነገር ያደረገ የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ነው” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “ይህን ያደረገ ማን ነው?” በማለት እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ። ነገሩን በጥብቅ ሲከታተሉም፣ “የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን መሆኑን ደረሱበት።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፥ “ይህን ያደረገ ማን ነው?” በማለት እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ። ነገሩን በጥብቅ ሲከታተሉም፥ “የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን መሆኑን ደረሱበት።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስ በርሳቸውም “ይህን ያደረገ ማን ነው?” በማለት ተጠያየቁ፤ ብዙ ከተመራመሩም በኋላ ይህን ያደረገው የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን መሆኑን ደረሱበት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስ በርሳቸውም፦ ይህን ነገር ያደረገ ማን ነው? ተባባሉ። በጠየቁና በመረመሩም ጊዜ፦ ይህን ነገር ያደረገ የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ነው አሉ። |
የከተማውም ሰዎች ማልደው ተነሡ፤ እነሆም፥ የበዓል መሠዊያ ፈርሶ፥ በዙሪያውም ያለው የማምለኪያ ዐጸድ ተቈርጦ፥ በተሠራውም መሠዊያ ላይ ሁለተኛው በሬ ተሠውቶ አገኙት።
የከተማዉም ሰዎች ኢዮአስን፥ “የበዓልን መሠዊያ አፍርሶአልና፥ በዙሪያውም ያለውን የማምለኪያ ዐጸድ ቈርጦአልና ይገደል ዘንድ ልጅህን አምጣ” አሉት።