በኮረብታም ያሉትን መስገጃዎች አስወገደ፤ ሐውልቶችንም ሰባበረ፤ የማምለኪያ ዐፀዶችንም ነቃቀለ፤ የእስራኤል ልጆች እስከዚህ ዘመን ድረስ ያጥኑለት ነበርና ሙሴ የሠራውን የናሱን እባብ አጠፋ፤ ስሙንም “ነሑስታን” ብሎ ጠራው።
መሳፍንት 6:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከተማውም ሰዎች ማልደው ተነሡ፤ እነሆም፥ የበዓል መሠዊያ ፈርሶ፥ በዙሪያውም ያለው የማምለኪያ ዐጸድ ተቈርጦ፥ በተሠራውም መሠዊያ ላይ ሁለተኛው በሬ ተሠውቶ አገኙት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሊቱ ነግቶ የከተማው ሕዝብ ከመኝታው ሲነሣ፣ የበኣል መሠዊያ ፈርሶ በአጠገቡ የቆመው የአሼራ ምስል ተሰባብሮ፣ አዲስ በተሠራው መሠዊያ ላይ ሁለተኛው ወይፈን ተሠውቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሊቱ ነግቶ የከተማው ሕዝብ ከመኝታው ሲነሣ፥ የበኣል መሠዊያ ፈርሶ በአጠገቡ የቆመው የአሼራ ምስል ተሰባብሮ፥ አዲስ በተሠራው መሠዊያ ላይ ሁለተኛው ወይፈን ተሠውቶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ የከተማይቱ ኗሪዎች ማልደው በተነሡ ጊዜ ለባዓል የተሠራው መሠዊያ መፍረሱንና የአሼራም ምስል ተሰባብሮ መውደቁን አዩ፤ ከዚያም በተሠራው መሠዊያ ላይ ሁለተኛው ኰርማ ታርዶ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ መቅረቡን ተመለከቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከተማውም ሰዎች ማልደው ተነሡ፥ እነሆም፥ የበኣል መሠዊያ ፈርሶ፥ በዙሪያው ያለውም የማምለኪያ ዐፀድ ተቈርጦ፥ በተሠራውም መሠዊያ ላይ ሁለተኛው በሬ ተሠውቶ አገኙት። |
በኮረብታም ያሉትን መስገጃዎች አስወገደ፤ ሐውልቶችንም ሰባበረ፤ የማምለኪያ ዐፀዶችንም ነቃቀለ፤ የእስራኤል ልጆች እስከዚህ ዘመን ድረስ ያጥኑለት ነበርና ሙሴ የሠራውን የናሱን እባብ አጠፋ፤ ስሙንም “ነሑስታን” ብሎ ጠራው።
ጌዴዎንም ከባሪያዎቹ ዐሥራ ሦስት ሰዎችን ወስዶ እግዚአብሔር እንዳለው አደረገ፤ የአባቱንም ቤተ ሰቦች፥ የከተማዉንም ሰዎች ስለፈራ ይህን በቀን ለማድረግ አልቻለም፤ ነገር ግን በሌሊት አደረገው።
እርስ በርሳቸውም፥ “ይህን ነገር ያደረገ ማን ነው?” ተባባሉ። በጠየቁና በመረመሩም ጊዜ፥ “ይህን ነገር ያደረገ የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ነው” አሉ።
ሳሙኤልም አንድ የበግ ጠቦት ወስዶ ለእግዚአብሔር ፈጽሞ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ከሕዝቡ ጋር አቀረበው፤ ሳሙኤልም ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው።