እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፥ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። አብራምም ለእርሱ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ መሠውያን ሠራ።
መሳፍንት 6:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌዴዎንም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም እስከ ዛሬ ድረስ “የእግዚአብሔር ሰላም” ብሎ ጠራው። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ ለኤዝሪ አባት በሆነችው በኤፍራታ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌዴዎንም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም “እግዚአብሔር ሰላም ነው” ብሎ ጠራው፤ ይህ መሠዊያ የአቢዔዝራውያን ይዞታ በሆነው በዖፍራ ዛሬም ቆሞ ይታያል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌዴዎንም በዚያ ለጌታ መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም “ጌታ ሰላም ነው” ብሎ ጠራው፤ ይህ መሠዊያ የአቢዔዝራውያን ይዞታ በሆነው በዖፍራ ዛሬም ቆሞ ይታያል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌዴዎንም በዚያ መሠዊያ ሠርቶ “እግዚአብሔር የሰላም አምላክ ነው” ብሎ ሰየመው፤ (ይህም መሠዊያ እስከ ዛሬ የአቢዔዜር ጐሣ ይዞታ በሆነችው በዖፍራ ቆሞ ይገኛል።) መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌዴዎንም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፥ ስሙንም፦ እግዚአብሔር ሰላም ብሎ ጠራው። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ ለአቢዔዝራውያን በምትሆነው በዖፍራ አለ። |
እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፥ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። አብራምም ለእርሱ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ መሠውያን ሠራ።
ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፤ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ፥ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ፤ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ።
በዚያም ዳዊት ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትንም አቀረበ። ሰሎሞንም በኋላ ዘመን በመሠዊያው ላይ ጨመረ፤ ያንጊዜ አነስተኛ ነበርና። እግዚአብሔርም ስለ ሀገሪቱ የተለመነውን ሰማ፤ መቅሠፍቱም ከእስራኤል ተከለከለ።
ድንጋዮችንም በእግዚአብሔር ስም መሠዊያ አድርጎ ሠራቸው፤ የፈረሰውንም መሠዊያ አደሰ፤ በመሠዊያውም ዙሪያ ሁለት መስፈሪያ እህል የሚይዝ ጕድጓድ ቈፈረ።
የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ፥ ወንድሞቹም ካህናቱ፥ የሰላትያልም ልጅ ዘሩባቤል፥ ወንድሞቹም ተነሥተው በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡበት ዘንድ የእስራኤልን አምላክ መሠዊያ ሠሩ።
በዘመኑም ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፤ ይህም ስም እግዚአብሔር በነቢያት ኢዮሴዴቅ ብሎ የጠራው ነው።
በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል፤ ኢየሩሳሌምም ተዘልላ ትቀመጣለች፤ የምትጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው።
ዙሪያዋም ዐሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፥ ከዚያም ቀን ጀምሮ የከተማዪቱ ስም፦ ‘እግዚአብሔር በዚያ አለ’ ተብሎ ይጠራል።”
በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ ዮርዳኖስ አቅራቢያም ወደ ገለዓድ በመጡ ጊዜ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዚያ በዮርዳኖስ አጠገብ የሚታይ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ።
ጌዴዎንም ምስል አድርጎ ሠራው፤ በከተማውም በኤፍራታ አኖረው፤ እስራኤልም ሁሉ ተከትሎ አመነዘረበት፤ ለጌዴዎንና ለቤቱም ወጥመድ ሆነ።
የኢዮአስም ልጅ ጌዴዎን በመልካም ሽምግልና ሞተ፤ በአብያዜራውያንም ከተማ በኤፍራታ በነበረችው በአባቱ በኢዮአስ መቃብር ተቀበረ።
ቤቱም በዚያ ነበረና ወደ አርማቴም ይመለስ ነበር፤ በዚያም በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።