መሳፍንት 21:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማኅበሩም ሁሉ በሬሞን ዐለት ወዳሉት ወደ ብንያም ልጆች መልእክተኞችን ላኩ፤ በሰላምም ጠሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ጉባኤው በሙሉ በሬሞን ዐለት ወዳሉት ብንያማውያን የሰላም ጥሪ አስተላለፈ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ጉባኤው በሙሉ በሬሞን ዐለት ወዳሉት ብንያማውያን የሰላም ጥሪ አስተላለፈ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ መላው ጉባኤ የሪሞን አለት ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ወደነበሩት ብንያማውያን መልእክት ልከው ጦርነቱ እንዲቆም ተስማሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኅበሩም ሁሉ በሬሞን ዓለት ወዳሉት ወደ ብንያም ልጆች መልክተኞችን ላኩ፥ በዕርቅ ቃልም ተናገሩአቸው። |
ከእነርሱም የተረፉት ተመልሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፤ ከእነርሱም በየመንገዱ ላይ አምስት ሺህ ሰውን ለቀሙ፤ ወደ ጊድዓምም አሳደዱአቸው፤ ከእነርሱም ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደሉ።
በኢያቢስ ገለዓድ በሚኖሩ መካከልም ወንድ ያላወቁ አራት መቶ ቆነጃጅት ደናግልን አገኙ፤ በከነዓንም ሀገር ወዳለችው ወደ ሴሎ ወደ ሰፈሩ አመጡአቸው።
በዚያም ጊዜ የብንያም ልጆች ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፤ የእስራኤልም ልጆች ከኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ያዳኑአቸውን ሴቶች ሰጡአቸው። በዚህም ተስማሙ።