እኔ፥ ከእኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተማዪቱ እንቀርባለን፤ የጋይም ሰዎች እኛን ሊገናኙ እንደ ፊተኛው በወጡ ጊዜ ከፊታቸው እንሸሻለን፤
መሳፍንት 20:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብንያምም ልጆች፥ “እንደ ቀድሞው በፊታችን ይሞታሉ” አሉ። የእስራኤል ልጆች ግን፥ “እንሽሽ፤ ከከተማም ወደ መንገድ እናርቃቸው” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብንያማውያኑ፣ “እንደ በፊቱ ይኸው ድል እያደረግናቸው ነው” አሉ፣ እስራኤላውያንም በበኩላቸው፣ “ወደ ኋላ እያፈገፈግን ከከተማዪቱ ወደ መንገዶቹ እንዲርቁ እናድርጋቸው” ይሉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብንያማውያኑ፥ “እንደ በፊቱ ይሄው ድል እያደረግናቸው ነው” አሉ፥ እስራኤላውያንም በበኩላቸው፥ “ወደ ኋላ እያፈገፈግን ከከተማይቱ ወደ መንገዶቹ እንዲርቁ እናድርጋቸው” ይሉ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብንያማውያንም “ልክ ከዚህ በፊት እንዳደረግነው ፈጀናቸው” አሉ። እስራኤላውያን ግን “ወደ ኋላ አፈግፍገን ከከተማው ወደ አውራ ጐዳናው እናስወጣቸው” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብንያምም ልጆች፦ እንደ ቀድሞው በፊታችን ተመቱ አሉ። የእስራኤል ልጆች ግን፦ እንሽሽ፥ ከከተማም ወደ መንገድ እንሳባቸው አሉ። |
እኔ፥ ከእኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተማዪቱ እንቀርባለን፤ የጋይም ሰዎች እኛን ሊገናኙ እንደ ፊተኛው በወጡ ጊዜ ከፊታቸው እንሸሻለን፤
ወጥተውም በተከተሉን ጊዜ ከከተማ እናርቃቸዋለን፤ እነርሱም እንደ በፊቱ ከፊታችን ሸሹ ይላሉ፤ እኛም ከፊታቸው እንሸሻለን።
የብንያምም ልጆች በሕዝቡ ላይ ወጡ፤ ከከተማዪቱም ሸሹ፤ እንደ ቀድሞውም ጊዜ፥ በአውራዎቹ መንገዶች፥ አንደኛው ወደ ቤቴል፥ ሁለተኛውም ወደ ገባዖን ሜዳ በሚወስዱት መንገዶች ላይ ሕዝቡን ይመቱ፥ ይገድሉም ጀመር፤ ከእስራኤልም ሠላሳ የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ።
የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ከስፍራቸው ተነሥተው በበዓልታምር ተዋጉ። ከእስራኤልም አድፍጠው የነበሩት ከስፍራቸው ከገባዖን ምዕራብ ወጡ።
የእስራኤልም አርበኞች ከሰልፉ ተመለሱ፤ ብንያማውያንም እንደ ቀድሞው ሰልፍ በፊታችን ተመትተዋል እያሉ ከእስራኤል ሰዎች ሠላሳ የሚያህሉ ሰዎችን መምታትና መግደል ጀመሩ።