ኢዮአብም የቈጠራቸውን የሕዝቡን ድምር ለዳዊት ሰጠ፤ ከእስራኤልም ሁሉ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ተገኙ፤ ከይሁዳም አራት መቶ ሰባ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ተገኙ።
መሳፍንት 20:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብንያምም ልጆች ሌላ የእስራኤል ሰዎች አራት መቶ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ተቈጠሩ፤ እነዚህም ሁሉ ሰልፈኞች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን፣ ብንያማውያንን ሳይጨምር፣ ሰይፍ የታጠቁ አራት መቶ ሺሕ ተዋጊዎች አሰባሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያን፥ ብንያማውያንን ሳይጨምር፥ ሰይፍ የታጠቁ አራት መቶ ሺህ ተዋጊዎች አሰባሰቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን የብንያምን ነገድ ሳይጨምሩ ብዛቱ አራት መቶ ሺህ መሣሪያ የታጠቀ ሠራዊት አሰለፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብንያምም ልጆች ሌላ የእስራኤል ሰዎች አራት መቶ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ተቈጠሩ፥ እነዚህም ሁሉ ሰልፈኞች ነበሩ። |
ኢዮአብም የቈጠራቸውን የሕዝቡን ድምር ለዳዊት ሰጠ፤ ከእስራኤልም ሁሉ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ተገኙ፤ ከይሁዳም አራት መቶ ሰባ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ተገኙ።
ከእነዚያም ሕዝብ ሁሉ ሰባት መቶ የተመረጡ፥ ሁለቱም እጆቻቸው ቀኝ የሆኑላቸው ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህም ሁሉ ድንጋይ ይወነጭፉ ነበር፤ አንዲት ጠጕርስ እንኳ አይስቱም ነበር።
የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርንም፥ “የብንያምን ልጆች ለመውጋት መሪ ሆኖ ማን ይውጣልን?” ብለው ጠየቁት፤ እግዚአብሔርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤
ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ የሕዝቡ ሁሉ አለቆች ሰይፍ በሚመዝዙ፥ በቍጥርም አራት መቶ ሺህ እግረኞች በሆኑ በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ።