ኢዮርብዓም ግን በስተኋላቸው ይመጣባቸው ዘንድ ድብቅ ጦር አዞረባቸው፤ እነርሱ በይሁዳ ሰፈር ፊት ሳሉ ድብቅ ጦሩ በስተኋላቸው ከበባቸው።
መሳፍንት 20:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብንያምም ልጆች ከእስራኤል ልጆች ጋር ሊዋጉ ከየከተማዎቻቸው ወደ ገባዖን ተሰበሰቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እስራኤላውያንን ለመውጋት ከየከተሞቻቸው በአንድነት ወደ ጊብዓ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ እስራኤላውያንን ለመውጋት ከየከተሞቻቸው በአንድነት ወደ ጊብዓ መጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲያውም እነርሱን ለመውጋት ከብንያም ከተሞች ሁሉ ተሰባስበው ወደ ጊብዓ መጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብንያምም ልጆች ከእስራኤል ልጆች ጋር ሊዋጉ ከየከተማው ወደ ጊብዓ ተሰበሰቡ። |
ኢዮርብዓም ግን በስተኋላቸው ይመጣባቸው ዘንድ ድብቅ ጦር አዞረባቸው፤ እነርሱ በይሁዳ ሰፈር ፊት ሳሉ ድብቅ ጦሩ በስተኋላቸው ከበባቸው።
ሴዎንም እስራኤል በወሰኑ ላይ ያልፉ ዘንድ አልፈቀደም፤ ሴዎንም ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፤ እስራኤልንም ለመውጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፤ ወደ ኢያሶንም መጣ፤ እስራኤልንም ተዋጋቸው።
“አሁንም በገባዖን ውስጥ የበደሉ የዐመፅ ሰዎችን እንድንገድላቸው አውጥታችሁ ስጡን፤ ከእስራኤልም ልጆች ክፋትን እናርቃለን።” የብንያም ልጆች ግን የወንድሞቻቸውን የእስራኤልን ልጆች ቃል ሊሰሙ አልወደዱም።
በዚያም ቀን ከየከተማው የመጡ የብንያም ልጆች ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸውም ከገባዖን ሰዎች ሌላ ሃያ አምስት ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከገባዖንም ሰባት መቶ የተመረጡ ሰዎች ተቈጠሩ፤